የዱቄት ወተት ተፈላጊነት እና እጥረት ምክንያት፣ United States Department of Agriculture (USDA፣ የዩናይትድ ስቴትስ የግብርና መምሪያ) ለ Women, Infants, and Children (WIC፣ ሴቶች፣ ጨቅላ ህጻናት እና ህፃናት ልዩ ተጨማሪ የአመጋገብ ፕሮግራም) አንዳንድ ጊዜያዊ የዱቄት ወተቶችን እንዲያቀርብ ፈቅዷል። ወደ WIC የዱቄት ወተት (Similac) መመለስ አለብን። እባክዎ አዳዲስ ዝማኔዎችን ለመፈተሽ በ WIC የተፈቀደ የሕጻናት የዱቄት ወተት ድረ-ገጽን ይጠቀሙ።
አዲስ በ WIC የተፈቀደ የሕጻናት የዱቄት ወተት ለማየት አስፈላጊ ቀናት፦
- ማርች 1፣ 2023
- ሜይ 1፣ 2023
- ጁላይ 1፣ 2023
ልጅዎ በጊዜያዊ የዱቄት ወተት ላይ ከሆነ፣ ክሊኒካችሁ ስለምንሰጣቸው የ WIC የዱቄት ወተት አማራጮች ከእርስዎ ጋር ይነጋገራል።